Wellcome to the official blogger page of getachewbulti. This is getachewbulti official blogger page. Dedicated to posting my ideas,pictures, videos & vines of ethiopian's to show off our beauty and culture contributions are Wellcome.
Tuesday, 3 March 2015
Mr.Master killer
Saturday, 28 February 2015
ውሻ በበላችበት ነው የሚትጮህ!
የአገራችን የመብራት ችግር መቼ ነው የሚቀረፈው?
አገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት 20(ሃያ) ዓመታት ውስጥ ዘርፈ- ብዙ የልማት ዕድገት በማስመዝገብ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም አገር በአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ስነገረን ከርሟል ። ኢትዮጵያ ካስመዘገበችው ዕድገት ውስጥ ዋነኛው የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ዋነኛው ነው ።እነሱም የመንገድ ፣ የትምህርት ቤት ፣ የጤና ፣ የመጠጥ ውሃ ፣ የኃይል አቅርቦት ፣ የግብርና እና ሌሎችም የሚጠቀሱ መሰረተ ልማት ዕድገት በማስመዝገብ ረገድ የማይናቅ ሥራ ተሰርቷል ። በተለይ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የመንግሥትን ሥልጣነ በትሩን ከተቆናጠጠ ከ1983 ወዲህ አገርቷ የነበራትን 600 እስከ 800 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ሀብቷ በአሁኑ ጊዜ ታላቁን የሕዳሴ ግድብ ሳይጨምር ወደ 3500 ሜጋ ዋት አከባቢ አድርሳለች ።ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠቱን ስጀምር ይህ አገራችን ኢትዮጵያ አሁን ያላትን የኤሌክትሪክ ኃይሏን ወደ 10,000 ሜጋ ዋት ያድጋል ። በዚህ የኤሌክትሪክ ኃይል ሃብታችን በአፍሪካ ቀዳሚ ከማድረጉም በላይ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ከሃይሉ ሽያጭ ሊያስገኝልን እንደሚችል የብዙዎቻችን ግምት ነው ። በዚህ መጣጥፌ ስለአገራችን የኤሌክትሪክ ኃይል ሃብት ለመመስከር ፈልጌ ሳይሆን የዚህ ሃብት ባለቤት የማይቀረፍ ችግር የህዝቦቿ ብሶት እየሆነ መምጣቱን ለመግለጽ ፈልጌ ነው ። ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው በተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ምክንያቶ
የሳምንታት ክፍፍል
የሳምንታት ክፍፍል ሁሌም እንደተለመደው ከሥራዬ መልስ እቤቴ ሁኜ ከተለያዩ ምንጭ የሚተላለፉ መረጃዎች አከታተላለሁ ። ከዕለታት አንድ ቀን የተገነዘብኩት መረጃ ትኩረቴን ሳበና አንድ ነገር ለማለት ፈለኩት ። ነገሩ እንዲህ ነው የዓለማችን ሁለተኛዋ ግዙፉ የኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ቻይና የ 2014 ኢኮኖሚዋ መውረዱን እና ይህ ከ 18 ዓመት ወደዚህ ዝቅተኛ ሆኖ የተመዘገበ መሆኑን የሚዘግብ ዜና ነበር ። ዜናው በመቀጠል በዚህ በሩብ ዓመት ደግሞ 1.7%ኢኮኖሚዋ ማደጉን ተዘግቧል ።የቻይና ኢኮኖሚ በእንዱስትር ፣ በግብርና ፣በውጭ ንግድ እና በግንባታ ሥራ ላይ የተመሰረተ ሆኖ ዛሬ ከአሜሪካ ቀጥላ በሁለት ትርሊዬን ዶላር ሃብት በዓለማችን በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ። ይችህ ኢኮኖሚዋ በተለያየ ነገር ላይ የተመሰረተ ቻይና የዓመት ዕድገቷ 1.7%ብቻ ከሆነ እንደ አፍሪካ ያሉ ደሃ አገሮች ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገታቸው ምን ያህል እንደሆነ ለመገመት የግድ የኢኮኖሚ ባለሙያ መሆን አያስፈልግም ። ይህንን ለማለት የፈለኩት የአገራችን መሪዎች በእየዓመቱ የኢኮኖሚ ዕድገታችን 11.3%በላይ መሆኑን እየገለጹ ስለሆነ ነው ። በእርግጥ አገራችን ኢትዮጵያ ከ 18 ዓመት ወዲህ ፈጣን የሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ላይ እንደሆነች የሚካድ ሃቅ ነው ። ዛሬ ስለ አገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት ለመጻፍ ሳይሆን የዜጎቻችን አንድ አካል የሆነው የመንግሥት ሠራተኞች በኑሮ ውድነት መማረር አስመልክቶ አንድ የሰማውት ጨዋታ ስላስገረመኝ ላጋራችው ወደድኩኝ ። አንድ ወዳጄ የአገራችን የመንግሥት ሠራተኞች ውስጥ 95% ኑሮ በጣም ስለከበደው በወር ውስጥ ያሉትን ሳምንታት በመከፋፈል ስም ሰይመውለታል አለኝ ።እነሱም የወሩ መጀመሪያ ላይ የሚገኙ ማለትም ከ 30-10 ያሉ ቀናቶች ደመወዝ የሚወጣበት ሳምንት ስለሆነ ይህንን ሳምንት የፋስካ ሰሞን ይሉታል ።በዚህ ሰሞን ደመወዝ ስለምወጣ ሁሉም ዕዳውን ከፋፍሎ በተረፈችው ቀሪ ገንዘብ በቀን አንድ ጊዜ እንኳ ቢሆን የሚጣፍጥ ነገር ይበላል ።ስለዚህ ይህንን ሰሞን የፋስካ ሰሞን ይሉታል ። የወሩ 11ኛ ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ቀን ያሉትን ቀናት ደግሞ የኦዲት ሰሞን ይሉታል ይህ ሰሞን ለደመወዝ ስንት ቀን ቀረ ፣ በእጅ ላይ ያለው ገንዘብ ስንት ነው በማለት የሚያሰላበት ሰሞን ነው ። ሦስተኛው እና የመጨረሻው ሰሞን ደግሞ ከወሩ 21ኛው ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን ያሉት ቀናቶች ደግሞ የውዳዴ ሰሞን ይሉታል ።በዚህ ሰሞን አንድም ሠራተኛ በእጁ ላይ ምንም ገንዘብ ስለማይኖር ነው ። በዚህ ላይ አንድ ሁላችንም የምንገነዘበው ነገር በአገራችን ውስጥ ያሉ አብዛኛው የመንግሥት ሠራተኞች አሁን እየተከፈለው ያለ ደመወዝ ከአስር ቀናት በላይ ሊያስተዳድረው እንደማይችል ያሳየናል ። ወደፊትስ እንዴት ይዘልቃል ? እስቲ የራሳችውን አስተያየት ሥጡበት ።
Monday, 23 February 2015
ማስጠንቀቂያ አዘል በዓል
ሰሞኑን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ሙሉ የአየር ጊዜያቸውን በሕወሓት 40 ኛ የምስረታ በዓል ላይ ስያወሉ ነበር ። ህወሓት ትጥቅ ትግልን የጀመረበት 40ኛ ዓመት ማክበር የጀመረው የየካትቲ ወር መግቢያ ጀምሮ በተለያየ ቦታ እና በተለያየ ዝግጅት ማለትም በፓናል ውይይት ፣ በፎቶ እግዝብት ፣ በስፖርት ውድድር እና በሙዚቃ ከደደቢት እስከ ሐዋሳ ከሐረር እስከ ጅማ ስያከብር ከቆየ ቦኋላ ከየካቲት 10 ቀን ማለትም ከዋዜማው ጀምሮ እስከ የካቲት 11ቀን 2007 ማታ በደማቅ ሥነሥርዓት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ፣ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ፣ የክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች ፣ አጋር ድርጅቶች ተወካዮች ፣ የተለያየ አገራት መሪዎች ፣ አህጉራዊ እና የዓለም አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች በተገኙበት አክብሯል ።
ህወሓት በዚህ 40ኛ ዓመት ምስረታ በዓሉ ላይ በድርጅቱ ሥልጣን ዘመን የተመዘገቡ ድሎች እና የተገኙ የልማት ፣ የዴሞክራሲ ፣ የኢኮኖሚ ፣ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ውጤቶች በእግዝብሽን መልክ ቀርቦ ታይቷል ።
ህወሓት ሥልጣን ከያዘ ወዲህ በክልሉ ውስጥ የተገነቡ ትላልቅ እንዱስትሪዎች ፣ የተስፋፉ መሰረተልማቶች ፣ ሰማይ ጠቀስ እና ግዙፍ ህንፃዎች ስንመለከተው ክልሉ በሁሉም ረገድ ከሌሎች የአገርቷ ክልሎች የዛሬ 20 ዓመት ሊደርሱበት የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሷን እንገነዘባለን ።
ህወሓት በሥልጣን ዘመኑ በክልሉ ውስጥ ያስመዘገበው ዕድገት ላይ ምንም ቅሬታ የለኝም ። ሌሎች ክልሎች ለምን ከትግራይ ክልል ጋር በእኩል አላደረጉምም የሚል ጥያቄም የለኝም ። ምክንያቱም የትግራይ ክልል አመራሮች ትልቁና እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ አልፎ የመጡ ስለሆነ ትላንትና ከአጠገባቸው የተሰው ጓዶቻቸው አደራ የሰጡት የድርጅቱ ዓላማ ከዳር ለማድረስ በታማኝነት ስለሚሰሩ ነው ። የሌሎች ክልሎች አመራሮች ግን ኃላፊነቱን የተረከቡት ከሞቀ ቤታቸው ተጠርተው ስለሆነ ግድ የላቸውም ።
ወደ ህወሓት 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበር ሲንመለስ ህወሓት በዚህ በዓል ላይ ያወጣው ወጭ ምን ያህል ነው? እርግጠኛ ነኝ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘብ አፍሷል። ሌላው ቀርቶ ኢቢሲ ከመደበኛ ፕሮግራሙ በቀን ከአየር ሽያጭ እና ከማስታወቂያ የሚያገኘውን በዚህ ምክንያት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘብ እንደሚያጣ እናውቃለን ።
ይሁን! በዚህ ቀን እና ቀድሞ በነበረው ተከታታይ ቀኖች በድርጅቱ የቀድሞ እና ነባር ታጋዮች ስያስተላልፉት የነበረው የድርጅቱን ምስረታ ጀምሮ እስከ ዛሬ የነበሩትን ረጅም ጉዞ አስመልክቶ ሲሰጡ የነበረው መግለጫ የነበረውን እውነታ ብቻም ሳይሆን ማስጠንቀቂያ አዘል ነበር ።ይሄም "ሥልጣን የሚገኘው በትጥቅ ትግል እና በመሰዋሃት ብቻ እንደሆነ እና ሰላማዊ ትግል እና ምርጫ ቦታ እንደሌለው "ተናግረዋል ።ስለዚህ ሥልጣን ፈላጊዎች መልህክቱ ለእናንተ ነውና አርፋችሁ ተቀመጡ ።

Sunday, 15 February 2015
የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲነት!
የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲነት ።
ውድ አንባቢዎች በመጀመሪያ እንደምን ሰነበታችውልኝ ?በመቀጠል ለዛሬ ይችህን "የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲነት "የሚለውን አጭር ጹሑፍ ይዤላችሁ መጥቻለሁ እና በጥሞና ተከታተሉኝ ።
ጹሑፉ የገዳ ሥርዓት ምንነት የሚለውን ፅንሰ _ሃሳብ (concept )እና በገዳ እና ሥርዓቱ ላይ የተለያዩ የታርክ ፀሐፊዎች ( Antiyopology)ያሉትን እናያለን ።በመቀጠል የገዳ ዴሞክራሲነት ከነባራዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እንዴት እንደሚገለፅ በጥቅቱ አይተን ምሁራኖች በሰጡት አስተያየት ተነስተን ዘመናዊ ዴሞክራሲ እና የገዳ ሥርዓት ተመሣሣይነት እና ልዩነት ምን እንደሆነ እናያለን ፣ቀጥሎም የገዳ ሥርዓት በፓርላመንታዊ እና ፕሬዚዳንታዊ ዴሞክራሲ ውስጥ ምን ዓይነት ድርሻ እንዳለው አይተን ጹሑፉን እቋጫለሁ ።
ምዕራፍ ፩
ገዳ
ገደ ማለት ምን ማለት ነው? ይህንን ጥያቄ ለመመለስ Amin የተባለ አንድ ፀሐፊ መሐመድ ሐሰን የተባለ የቦረና ኦሮሞ ዋቢ በመጥቀስ እንዴፃፈው "ገዳ ማለት ከለላ ወይም ጥላ በመባል ከሚታወቅ ቃል የመጣ ነው "በማለት ይገልፃል ።
ፀሐፊው እንደገለፀው ይህ ከለላ ወይም ጥላ በሚባለው ቃል ሦስት ትርጉም በውስጡ ያካትታል ።እነሱም 1ኛ መጠለያ (Shelter ) ፣ 2ኛ መሸሸጊያ (for taking refuge )፣ 3ኛ ጥላ ወይም በኦሮሞ ቋንቋ Guddisa የሚባለው (Umbrella )እንደማለት ነው ።"ይላል ።
ከዚህ ትርጉም ውስጥ ከለላ ወይም ጥላ የሚለው ቃል ኦሮሞ የሚወደው እና የሚያከብረው በሥሩ ስለማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮቹን የሚወያይበት "ኦዳ " የሚባለው ታርካዊ እና ትልቁ ዛፍ ጋር ለማነፃፀር ተፈልጐ ነው ።
ያም ሆነ ይህ ገዳ እና ከለላ ወይም ጥላ ለማነፃፀር የተሞከረው ጽንሰ ሃሳብ የሚናቅ አይደለም ። በሌላ በኩል ግን አንዳንድ የአስትሮፖሎጂ ፀሐፊዎች ማለትም እንደ አስመሮም ለገሠ እና ባክስታር የመሳሰሉት " ገዳ ማለት ዘመን ፣ ዕድሜ እና ዓመት "እንደሆነ ይገልፃሉ ።ኦሮሞ ስንት ዓመት ነው በማለት ዕድሜ ይጠያየቃል ፣ ዘመንን ደግሞ ስንት ገዳ ነው በማለት ይጠያየቃል ። ስለዚህ ከላይ ፀሐፊዎች የሰጡት አስተያየት እና የህዝቡን ስንመለከተው "ገዳ ማለት ዕድሜ እና ዘመን መሆኑን እንረዳለን ።
ምዕራፍ 2
የገደ ሥርዓት (The Gada System )
የገደ ሥርዓት ምንነት ላይ ፀሐፊዎች የተለያየ አመለካከት አላቸው ።ከፊሎቹ "ገዳ ኦሮሞ ስለ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮቹን የሚመራበት ከባህሉ የመነጨ ሥርዓት ነው " በማለት ይገልፃሉ ።እንደ ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሠ ያሉ ጸሐፊዎች ደግሞ " ገዳ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሥርዓት ብቻም ሳይሆን ኦሮሞ ኢኮኖሚውን የሚመራበት ሥርዓትም ጭምር ነው "ይላሉ ።ፕየኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲነት በምን ይገለፃል ?
ፕሎዎድን የተባለ አንድ የታርክ ፀሐፊ የገዳ ሥርዓት ማንነት ስገልፅ "Among the Republican system ,Gada is superior "ትርጉሙም "ከማንኛውም ሪፑብልካዊያን በበለጠ ገዳ የበላይ ነው ።"ማለቱ ነው ።ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሠም ይህንን ሃሣብ ስያጠናክሩ "Gada System is one of the most astonishing & instructive turns the evolution of human society has taken "ትርጉሙም "የገዳ ሥርዓት በሰው ልጅ ዕድገት (evolution )ውስጥ አስደናቂ የሆነ ብዙ ታላላቅ ለውጦች የታየበት ሥርዓት ነው "በማለት ይገልፃል ።
ባክስታር የተባለ ፀሐፊ "ኦሮሞ አስደናቂ የገዳ ሥርዓት ቢኖረውም ዕድሜያዊ መዋቅር (age sets) የሆነ አስተዳደራዊ ሥልጣን የሌለው ፣ በፖለቲካዊ ጉዳዮች በቀጥታ የማይገናኝ ፣ በአስተዳደራዊ ጉዳይ ውስጥ ምንም ዓይነት ድርሻ እንደሌለው እና ግጭትን መፍታት እንደማይችል ይናገራል ።ይሁን እንጂ ብዙ ፀሐፊዎች ከባክስታ ሃሳብ ጋር አይስማሙም ።ምክንያቱም በገዳ ሥርዓት ውስጥ የሚገኙ የዱባሌ ፣ ታናናሽ ጋሜ ፣ ታላላቅ ጋሜ ፣ ኩሳ እና ራባ ገዳ የተባሉ ደረጃዎች ሳያልፍ ወደ አባገዳ ሥልጣን የሚመጣ አንድም የኦሮሞ ልጅ አይኖርም ።እነዚህ የገዳ ሥርዓት እርከኖች ለሥልጣን የሚታጩ ሰዎች ልምድ እንድያገኙ እና የገዳ ሥርዓት ሃላፊነት መሸከም እንድችሉ እና ራሳቸውን የሚያዘጋጁበት አድካም (rite of passage )ያለው እና በዓለምአቀፍ የተደነቀ ሥርዓት ነው ።ሮፌሰር አስመሮም ለገሠ ይህንን እንዲህ በማለት ይገልፃሉ " it is a system of classic (sets of );that succeed each other every eight years in assuming Military ,political & Economic ritual responsibilities of the Gada System is an institutional that represention extreme development of a type of social structure known ; anthropologist as age sets "ይላሉ ።ትርጉሙም " ገዳ የዕድሜ መዋቅር ሆኖ በእየ ስምንት ዓመት የሚቀባበሉት ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው ተቋም ያቀፈ ነው ።እንዴ አንትዮሮፖሎጂስቶች አገላለጽ በዕድሜ ላይ የተመሰረተ ትልቅ ዕድገት እና ከፍተኛ ሕዝባዊ መዋቅር የሚታይበት ሥርዓት ነው "ይላሉ ።እንዴ ፀሐፊው አባባል የኦሮሞ ፀጋ እና እምነት የሆነው ዋቄፈና በዚህ ሥርዓት ይመራል ።በተጨማሪም የኦሮሞ ፍልስፍና ግኝት እና ሕግ የሆነው የጊዜ መቁጠሪያ "ካላንደርም"ምንጩ ገዳ ሥርዓት እንደሆነ ይታሰባል ።ባኪስታሪ የተባለ ፀሐፊም"የገዳ ሥርዓት በቃል የሚገልፅ በተግባርም የሚታይ ፖለቲካዊ ፍልስፍና ነው ።" ይላል ።በአጭሩ የገዳ ሥርዓት ከኦሮሞ ባህል ውስጥ የመነጨ ሕግ ሆኖ ኦሮሞ እርስ በእርሱ የሚተዳደርበት እና የሚተዳደርበት ፣ መብቱን እና ግደታውን የሚለይበት ፣ አገሩን ፣ ኢኮኖሚውን እና እምነቱን የሚፈፅምበት ሃሣቡን የሚገልፅበት ፣ ፍላጎቱን የሚያሟላበት ሥርዓት ነው ።
ይሁን እንጂ ገዳ የኦሮሞ ብቻ ነው ?የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም ።እዚ ላይ መታወቅ ያለበት አንድ ነገር በደቡብ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ኩሽ ሕዝቦች ማለትም ሲዳማ ፣ ጌድኦ ፣ ወላይታ ፣ አዲያ ፣ ኮንሶ ...ወዘተ ልክ እንደ ኦሮሞ ገዳ የሰው ልጅ መሠረታዊ ኑሮ የሚያቅፍ ባይሆንም የራሳቸው የሆነ ገዳ ሥርዓት አላቸው ።እንዲሁም በሱዳን የኑዌር ሕዝብ በኬንያ ማሳዮታ እና ኩኩዩ ገዳ አላቸው ።
ይሁን እንጂ የገዳ ሥርዓት ምንጩ ከኦሮሞ ነው ወይስ ከኩሽ ነው ?የሚለው ጥያቄ ለምርምር ክፍት እናድርገው ።አንድ እውነታ ግን የገዳ ሥርዓት ኦሮሞ ዘንድ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በስፋት እና በጥልቀት ስመራበት እና ስሰራበት የኖሬ ሥርዓት ነው ።
የገዳ ሥርዓት እንዴት እና መቼ ተጀመረ ?የሚል ጥያቄ ልነሳ ይችላል ። የገዳ ሥርዓት መቼ እንደተጀመረ ከመቼ ጀምሮ ሥራ እንደዋለ ትክክል የሆኖ የተቀመጠ መረጃ ባይኖርም እንደኦሮሞ ታርክ መረጃ መሠረት ከ500 ዓመት በፊት ስሰራበት እንደነበረ ይገመታል ። ፕሮዊት የተባለ ፀሐፊ ሐሬሮ ከማታ የሚባል ታርክ አዋቂ የቦረና ኦሮሞ ዋቢ በመጥቀስ ከ4000 ዓመት ጀምሮ ኦሮሞ የገዳ ሥርዓት ስተዳደርበት እንደነበረ ገልፀዋል ።
ምህራፍ ሦስት
የገዳ ሥርዓት በምን ይገለፃል ?
አንድ ፕላዎድን የተባለ ፀሐፊ የገዳ ሥርዓት ማንነት ስገልፅ "Among the Republican system ,gada is superior " ከማንኛውም ሪፑብልካዊያን በበለጠ ገዳ የበላይ ነው ።ማለቱ ነው ።አስመሮም ለገሠም ይህንን ሃሳብ በማጠናከር "Gada System is one of the most astonishing & instructive turns the evolution of human society has taken "ትርጉሙም "የገዳ ሥርዓት በሰው ልጅ ዕድገት (evolution )ውስጥ አስደናቂ የሆነ ብዙ ታላላቅ ለውጦች የታየበት ሥርዓት ነው "በማለት ይገልፃል ።ባክስታር የተባለ ፀሐፊ "ኦሮሞ አስደናቂ የገዳ ሥርዓት ቢኖረውም ዕድሜያዊ መዋቅር (age sets) የሆነ አስተዳደራዊ ሥልጣን የሌለው ፣ በፖለቲካዊ ጉዳዮች በቀጥታ የማይገናኝ ፣ በአስተዳደራዊ ጉዳይ ውስጥ ምንም ዓይነት ድርሻ እንደሌለው እና ግጭትን መፍታት እንደማይችል ይናገራል ።ይሁን እንጂ ብዙ ፀሐፊዎች ከባክስታ ሃሳብ ጋር አይስማሙም ።ምክንያቱም በገዳ ሥርዓት ውስጥ የሚገኙ የዱባሌ ፣ ታናናሽ ጋሜ ፣ ታላላቅ ጋሜ ፣ ኩሳ እና ራባ ገዳ የተባሉ ደረጃዎች ሳያልፍ ወደ አባገዳ ሥልጣን የሚመጣ አንድም የኦሮሞ ልጅ አይኖርም ።እነዚህ የገዳ ሥርዓት እርከኖች ለሥልጣን የሚታጩ ሰዎች ልምድ እንድያገኙ እና የገዳ ሥርዓት ሃላፊነት መሸከም እንድችሉ እና ራሳቸውን የሚያዘጋጁበት አድካም (rite of passage )ያለው እና በዓለምአቀፍ የተደነቀ ሥርዓት ነው ። ስለዚህ የገዳ ሥርዓት የዕድሜ እና አስተዳደራዊ ቅንጅት የለውም የምል ሃሳብ ተቀባይነት የለውም ።
በአጭሩ በዚህ በገዳ ሥርዓት ውስጥ የሚታወቁ ታላላቅ ጉዳዮች የሥርዓቱ ዓላማ ከሪፑብልካዊያን ጋር መመሳሰሉ ነው ።
ምህራፍ አራት
የገዳ ሥርዓት እና የዴሞክራሲ ተመሳሳይነት እና ልዩነት ።
ከላይ የገዳ ሥልጡንነት መዳሰስእንደሞከርኩት ከአስትሮኖሚ አመለካከት በመነጨ የራሱ ካላንደር ፣ የራሱ የሆነ አስተዳደር የማህበራዊ አስተሳሰር እነደሆነ ይታወቃል ።ይሁን እንጂ ከአንዳንድ ሁኔታ የተነሳ የገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲ(classic democracy)ከዓለም ዴሞክራሲ ሥልጣኔ ጋር እንዳይራመድ እና ወደ አድሱ የዴሞክራሲ ግኝት እራሱን ማሳደግ(transcend)ማድረግ አልቻለም ።በተለያየ ጊዜ ብቅ ስሉ የነበሩት ገዥ መደቦች ሊያቀጭጩት እና ልያጠፉት ሞክሮ ነበር። ስለዚህ እንደ ምህራብያዊያኖች ሥልጣኔ(western civilization)ከሌሎች ዓለም ሥልጣነ የሚጠቅመውን በመውሰድ ራሱን አሻሽሎ እና አዳብሮ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር መራመድ አልቻለም። ሌሎች የዓለም ሃይማኖቶች ማለትም ክርስቲያን እና እስላም በቅደመተከተል በመግባት የምህራባዊያን ዴሞክራሲ(western democracy) እና የምስራቅያዊያን ዴሞክራሲ(Oriental democracy)መሰረት የሆነውን የራሳቸውን እምነት ለማስፋፋት ስባል ስፈፅሙበት የነበረው ድርጊት ለገዳ ሥርዓት ዕድገት ምቹ ሁኔታ አልፈጥረለትም። በዚህ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች የገዳ ሥርዓት ከዘመኑ ዴሞክራሲ ጋር ልዩነት እና ተመሳሳይነት ልኖረው ችሎአል ።
የገዳ ሥርዓት እና የዘመኑ ዴሞክራሲ ልዩነት
የገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲነት በሁለት ጎራ ተቀናጅተው በአካል እና በአህምሮ ዳብሮ (socialization process)አልፎ በሥልጣን ላይ ሃላፊነት መውሰድ መቻል አለበት።ይህ በምህራብዊያን ዴሞክራሲ ዘንድ ደካማ ነው ።
በገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲ classical ውስጥ ሥልጣን ለመያዝ ስባል ማመፅ እና የመገዳደል ባህል የለም ።እንዲሁም የአማባግሸን ባህልም የለም ።የፖለቲካ ሹመት እና ሥልጣን(authority)በእንስትውትሽናል(Institutional)በሆነ መንገድ ብቻ ነው ሥልጣን ከአንዱ ወደ አንዱ የሚተላለፈው ።ሥልጣን ከአንዱ ወደ አንዱ በሚተላለፍበት ወቅት ሥልጣን የሚያስተላልፈውም ሆነ ሥልጣን የሚቀበለው አባሎቻቸውን ከብት አርደው አብልቶ አጠጥተው ጨፍሮ አስጨፍሮ ቡታ ድግስ የሚባለውን ሥርዓት ላይ የፖለቲካ ሥልጣን የሚረካከቡት ።
የኦሮሞ ገዳ ዴሞክራሲ በዕድሜ ሁኔታ ማህበራዊ አደረጃጀት ያለው ሲሆን በዚህ አደረጃጀት ላይ ተንተርሶ መብት እና ግዴታ ይሰጣል ።
የዘመናዊው ዴሞክራሲ ግን እንደዚህ ዓይነት አደረጃጀት የለውም ።
የገዳ አባል በመሆን የፖለቲካ ፣ የወታደራዊ እና የዋቀፌታ እምነት ሃላፊነት መውሰድ የሚችል ወንድ ብቻ ነው ።ይህ ጉድለቱ ሲሆን በምህራብዊያን ዴሞክራሲ ዘንድ ግን በሁሉም ሃላፊነት ወንድ እና ሴት እኩል ናቸው ።
በምዕራብያዊያን ዴሞክራሲ የለሌው በኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ውስጥ የአባቶች ገዳ እና የልጆች ፓርቲ ገዳ በመባል በሁለት ተለይተው አለ ። ሁለቱም የራሱ የሆነ አምስት አምስት ፓርቲ አለው ።ለምሳሌ በቦረና ኦሮሞ ውስጥ የገዳ ሥልጣን ቢርመጅ ፣ መልባ ፣ ሙዳ፣ ሮበሌ ዱሎ የሚባሉ የአባቶች ገዳ ፓርቲ ስኖሩ እንዲሁም በልጆች ገዳ ፓርቲ ውስጥ ደግሞ አልዳዳ ፣ ኦራታ፣ ብፎሌ ፣ ሱቡቃ እና ክሎሌ የተባሉትን ፓርቲዎች አሉአቸው ።ሁለት ዙር (two sami cycles)40 ዓመት በፊት የአባቶች ገዳ ስሆን የቀረው 40 ዓመት ደግሞ የልጆች ገዳ ፓርቲ ይሆናል ። በምህራብዊያን ዴሞክራሲ ውስጥ ሃይማኖት እና መንግሥት (in principal )የተለያዩ ናቸው ።በገዳ ሥርዓት ግን ገዳ እና ቃሉ ይተጋገዛሉ።
የገዳ ሥርዓት እና የዘመኑ ዴሞክራሲ ተመሳሳይነት
ልክ እንደ ምህራብያዊያኖች ዴሞክራሲ የገዳ ሥርዓትም አስተዳዳሪዎቹን ለተወሰነ ጊዜ ይመርጣቸዋል ህዝቡ ነው የሚመርጣቸው የመመረጥ ብቃትም ወሳኝ ነው ።እንደአስፈላጊነቱ የህዝቡን መብት የማያስከብር ከሆነም የተመረጠውን ከሥልጣን የሚያወርደውም ሕዝቡ ነው ጠባቂም ይሾማል ።
የገዳ ሥርዓት ልክ እንደ ምህራብያዊያኖች ዴሞክራሲ አስተዳደራዊ መዋቅሩ እስከ ቀበሌ ድረስ አለው ።በቀበሌም በእየጎሳ ጠቅላላ ስብሰና(ጉባኤ)አለው ።ማንኛውም ሰው በተለያየ ጉባኤ ላይ ተሳትፎ ሃሳቡን በነፃነት ይገልፃል ።የፈለገውን ደግፎ የፈለገውን ለመቃወም ሙሉ መብት አለው ።በዚህ ረገድ ገዳ ሥርዓት እና የምህራባዊያን ዴሞክራሲ በጣም ይመሳሰላል ።
ሁለቱም ዴሞክራሲ የሕዝባቸውን መብት እና ግዴታ የሚደነግግ ሕግ አላቸው ።የገዳ ሥርዓት ህግ ልክ እንደ ምህራብያዊያኖች ዴሞክራሲ ሕግ የተፈጥሮ እንክብካቤ ሕግ አለው።የነፍስ ጥበቃም ሕይወት ላሌውም ለሌለውም (animate & inanimate object )የመሳሰሉት አሉት ።የሁለቱ ዴሞክራሲ መመሳሰል በዚህ አጭር ጹሑፍ መግለፅ ይከብዳል ።
ምህራፍ 5
የገዳ ሥርዓት በዘመኑ ዴሞክራሲ ውስጥ ልኖረው የሚችለው ሚና
ገዳ በአፍሪካ ቀንድ አከባቢ ለተለያየ ሁኔታ እና ዓላማ በጥቅም ላይ ሲውል እንደነበረ በትንሹም ቢሆን ለመጠቃቀስ ሞክረነዋል ።በኢትዮጵያ ውስጥም ኦሮሞ ፣ ሲዳማ ፣ ወላይታ ፣ ኮንሶ ፣ አዲያ ፣ ጌድኦ እና ወዘተ በኬንያ ውስጥ በእንደ መሳይ እና ኩኩዩ በሱዳን የኑዌር ሕዝብ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ ።
ይህንን የገዳ ሥርዓት እንደአስፈላጊነቱ በማጠናከር እና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ተሻሽሎ እንዲሰራበት ቢደረግ ለምስራቅ አፍርካ ህዝቦች ሠላም እና አብሮ መኖር ውስጥ የጎላ ሚና እንዳለው ይታመንበታል ።በአገር ውስጥም ለህዝቦች ሠላም እና መቀራረብ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ።ሥራ ወዳድ ዜጋ ፣የተነሳሽነት ፍላጎት ኖሮት ሠርቶ ራሱን ለማስተዳድር የሚችል በመፍጠር ረገድ በተለየ በኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ውስጥ ማላመድ (socialization process)በእየደረጃ የሚሄድ እንድጠናከር ማድረግ ትልቅ ውጤት አለው።በገዳ ሥርዓት ውስጥ ያለውን የመደማመጥ ባህል እና ሃሳቡን በነፃነት የመግለፅ መብት በቀጣይነት እንዲጠናከር በማድረግ ዴሞክራቲክ እና ዴሞክራሲን ለማሳደግ (ለማዳበር)ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ።
ለትግበራውም ትልቅ እና ጥልቀት ያለው ምርምር ማካሄድ ይጠበቃል ።የገዳ አባቶች የባህል መሪዎች ተከታታይነት ያለው ግኑኙነት መፍጠር አስፈላጊ ነው ።በተለያየ ጊዜ እና ቦታ የሚደረግ አገርአቀፍ እና ዓለምአቀፍ ጉባኤዎች ላይ የገዳ አባቶችን በማሳተፍ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የገዳ ሥርዓት ሕጎችን ተሻሽሎ እንዲሠራ ማድረግ አስፈላጊ ነው ።ለምሳሌ የቦረና ገዳ ብንመለከት በእየስምንት ዓመቱ የሚደረግ "ጉሚ ጋዮ"(Gumii Gaayyoo)የሚጠራ ጉባኤ አለ ።የዚህ "ጉሚ ጋዮ"ዓላማም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከወቅቱ ሁኔታ ጋ ሊዛመድ የማይችል ሕጎችን ለመሻር እና ጊዜው የሚጠይቅ አድስ ሕጎች ለመጨመር ታስቦ ነው ።
የገዳ ሥርዓት ጉባኤዎች በሃሳብ ፣ በገንዘብ ፣ በዕውቀት እና በማቴሪያል በማጠናከር መብት እና ግዴታ የሚደነግግ የባህል ህግ ወሰን ለማስከበር እርስ በእርሱ የገዳ ሥርዓት ሕጎችን (ዴሞክራሲን የሚያስታርቅ)ገምግመው ለመሻርም ሆነ ለማሻሻል እንዲችሉ ማገዝ አስፈላጊ ነው ።
Harbar Liws የተባለ ተመራማሪ እንዲህ በማለት ይገልፃል "In this connection utilizing or making creative use of gada System than trying to weaken or destroy it & it ...could play a vital role in the correct political life it nurture & permitted to flourished ""የገዳ ሥርዓት ለማጥፋት ወይም ለማስቀረት ከመልፋት ይልቅ ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ ሁኔታ በማዘጋጀት ባለው የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ እንድያብብ ፣ እንድጠናከር ማድረግ በጣም አስፈላጊ እና ለነገ የማይባል ጉዳይ ነው ።"ይላል ።