Saturday, 28 February 2015

የሳምንታት ክፍፍል

የሳምንታት ክፍፍል ሁሌም እንደተለመደው ከሥራዬ መልስ እቤቴ ሁኜ ከተለያዩ ምንጭ የሚተላለፉ መረጃዎች አከታተላለሁ ። ከዕለታት አንድ ቀን የተገነዘብኩት መረጃ ትኩረቴን ሳበና አንድ ነገር ለማለት ፈለኩት ። ነገሩ እንዲህ ነው የዓለማችን ሁለተኛዋ ግዙፉ የኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ቻይና የ 2014 ኢኮኖሚዋ መውረዱን እና ይህ ከ 18 ዓመት ወደዚህ ዝቅተኛ ሆኖ የተመዘገበ መሆኑን የሚዘግብ ዜና ነበር ። ዜናው በመቀጠል በዚህ በሩብ ዓመት ደግሞ 1.7%ኢኮኖሚዋ ማደጉን ተዘግቧል ።የቻይና ኢኮኖሚ በእንዱስትር ፣ በግብርና ፣በውጭ ንግድ እና በግንባታ ሥራ ላይ የተመሰረተ ሆኖ ዛሬ ከአሜሪካ ቀጥላ በሁለት ትርሊዬን ዶላር ሃብት በዓለማችን በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ። ይችህ ኢኮኖሚዋ በተለያየ ነገር ላይ የተመሰረተ ቻይና የዓመት ዕድገቷ 1.7%ብቻ ከሆነ እንደ አፍሪካ ያሉ ደሃ አገሮች ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገታቸው ምን ያህል እንደሆነ ለመገመት የግድ የኢኮኖሚ ባለሙያ መሆን አያስፈልግም ። ይህንን ለማለት የፈለኩት የአገራችን መሪዎች በእየዓመቱ የኢኮኖሚ ዕድገታችን 11.3%በላይ መሆኑን እየገለጹ ስለሆነ ነው ። በእርግጥ አገራችን ኢትዮጵያ ከ 18 ዓመት ወዲህ ፈጣን የሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ላይ እንደሆነች የሚካድ ሃቅ ነው ። ዛሬ ስለ አገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት ለመጻፍ ሳይሆን የዜጎቻችን አንድ አካል የሆነው የመንግሥት ሠራተኞች በኑሮ ውድነት መማረር አስመልክቶ አንድ የሰማውት ጨዋታ ስላስገረመኝ ላጋራችው ወደድኩኝ ። አንድ ወዳጄ የአገራችን የመንግሥት ሠራተኞች ውስጥ 95% ኑሮ በጣም ስለከበደው በወር ውስጥ ያሉትን ሳምንታት በመከፋፈል ስም ሰይመውለታል አለኝ ።እነሱም የወሩ መጀመሪያ ላይ የሚገኙ ማለትም ከ 30-10 ያሉ ቀናቶች ደመወዝ የሚወጣበት ሳምንት ስለሆነ ይህንን ሳምንት የፋስካ ሰሞን ይሉታል ።በዚህ ሰሞን ደመወዝ ስለምወጣ ሁሉም ዕዳውን ከፋፍሎ በተረፈችው ቀሪ ገንዘብ በቀን አንድ ጊዜ እንኳ ቢሆን የሚጣፍጥ ነገር ይበላል ።ስለዚህ ይህንን ሰሞን የፋስካ ሰሞን ይሉታል ። የወሩ 11ኛ ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ቀን ያሉትን ቀናት ደግሞ የኦዲት ሰሞን ይሉታል ይህ ሰሞን ለደመወዝ ስንት ቀን ቀረ ፣ በእጅ ላይ ያለው ገንዘብ ስንት ነው በማለት የሚያሰላበት ሰሞን ነው ። ሦስተኛው እና የመጨረሻው ሰሞን ደግሞ ከወሩ 21ኛው ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን ያሉት ቀናቶች ደግሞ የውዳዴ ሰሞን ይሉታል ።በዚህ ሰሞን አንድም ሠራተኛ በእጁ ላይ ምንም ገንዘብ ስለማይኖር ነው ። በዚህ ላይ አንድ ሁላችንም የምንገነዘበው ነገር በአገራችን ውስጥ ያሉ አብዛኛው የመንግሥት ሠራተኞች አሁን እየተከፈለው ያለ ደመወዝ ከአስር ቀናት በላይ ሊያስተዳድረው እንደማይችል ያሳየናል ። ወደፊትስ እንዴት ይዘልቃል ? እስቲ የራሳችውን አስተያየት ሥጡበት ።

No comments: