ሰሞኑን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ሙሉ የአየር ጊዜያቸውን በሕወሓት 40 ኛ የምስረታ በዓል ላይ ስያወሉ ነበር ። ህወሓት ትጥቅ ትግልን የጀመረበት 40ኛ ዓመት ማክበር የጀመረው የየካትቲ ወር መግቢያ ጀምሮ በተለያየ ቦታ እና በተለያየ ዝግጅት ማለትም በፓናል ውይይት ፣ በፎቶ እግዝብት ፣ በስፖርት ውድድር እና በሙዚቃ ከደደቢት እስከ ሐዋሳ ከሐረር እስከ ጅማ ስያከብር ከቆየ ቦኋላ ከየካቲት 10 ቀን ማለትም ከዋዜማው ጀምሮ እስከ የካቲት 11ቀን 2007 ማታ በደማቅ ሥነሥርዓት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ፣ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ፣ የክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች ፣ አጋር ድርጅቶች ተወካዮች ፣ የተለያየ አገራት መሪዎች ፣ አህጉራዊ እና የዓለም አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች በተገኙበት አክብሯል ።
ህወሓት በዚህ 40ኛ ዓመት ምስረታ በዓሉ ላይ በድርጅቱ ሥልጣን ዘመን የተመዘገቡ ድሎች እና የተገኙ የልማት ፣ የዴሞክራሲ ፣ የኢኮኖሚ ፣ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ውጤቶች በእግዝብሽን መልክ ቀርቦ ታይቷል ።
ህወሓት ሥልጣን ከያዘ ወዲህ በክልሉ ውስጥ የተገነቡ ትላልቅ እንዱስትሪዎች ፣ የተስፋፉ መሰረተልማቶች ፣ ሰማይ ጠቀስ እና ግዙፍ ህንፃዎች ስንመለከተው ክልሉ በሁሉም ረገድ ከሌሎች የአገርቷ ክልሎች የዛሬ 20 ዓመት ሊደርሱበት የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሷን እንገነዘባለን ።
ህወሓት በሥልጣን ዘመኑ በክልሉ ውስጥ ያስመዘገበው ዕድገት ላይ ምንም ቅሬታ የለኝም ። ሌሎች ክልሎች ለምን ከትግራይ ክልል ጋር በእኩል አላደረጉምም የሚል ጥያቄም የለኝም ። ምክንያቱም የትግራይ ክልል አመራሮች ትልቁና እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ አልፎ የመጡ ስለሆነ ትላንትና ከአጠገባቸው የተሰው ጓዶቻቸው አደራ የሰጡት የድርጅቱ ዓላማ ከዳር ለማድረስ በታማኝነት ስለሚሰሩ ነው ። የሌሎች ክልሎች አመራሮች ግን ኃላፊነቱን የተረከቡት ከሞቀ ቤታቸው ተጠርተው ስለሆነ ግድ የላቸውም ።
ወደ ህወሓት 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበር ሲንመለስ ህወሓት በዚህ በዓል ላይ ያወጣው ወጭ ምን ያህል ነው? እርግጠኛ ነኝ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘብ አፍሷል። ሌላው ቀርቶ ኢቢሲ ከመደበኛ ፕሮግራሙ በቀን ከአየር ሽያጭ እና ከማስታወቂያ የሚያገኘውን በዚህ ምክንያት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘብ እንደሚያጣ እናውቃለን ።
ይሁን! በዚህ ቀን እና ቀድሞ በነበረው ተከታታይ ቀኖች በድርጅቱ የቀድሞ እና ነባር ታጋዮች ስያስተላልፉት የነበረው የድርጅቱን ምስረታ ጀምሮ እስከ ዛሬ የነበሩትን ረጅም ጉዞ አስመልክቶ ሲሰጡ የነበረው መግለጫ የነበረውን እውነታ ብቻም ሳይሆን ማስጠንቀቂያ አዘል ነበር ።ይሄም "ሥልጣን የሚገኘው በትጥቅ ትግል እና በመሰዋሃት ብቻ እንደሆነ እና ሰላማዊ ትግል እና ምርጫ ቦታ እንደሌለው "ተናግረዋል ።ስለዚህ ሥልጣን ፈላጊዎች መልህክቱ ለእናንተ ነውና አርፋችሁ ተቀመጡ ።
Wellcome to the official blogger page of getachewbulti. This is getachewbulti official blogger page. Dedicated to posting my ideas,pictures, videos & vines of ethiopian's to show off our beauty and culture contributions are Wellcome.
Monday, 23 February 2015
ማስጠንቀቂያ አዘል በዓል
Labels:
current affair
Location:
Horn of Africa, null
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment