አንድ "አየለ ገመቹ "የተባለ ፀሐፊ በዘአበሻ ድረ ገፅ ላይ "የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ነፍጥ ሳይሆን ግልገል ነው"በሚል አርዕስት በፃፈው ፁሑፍ የኦሮሞ ውድ እና ብርቅዬ ልጅ በሆነው ጁሃር መሐመድ እና በኦሮሞ ህዝብ ላይ አድስ የስም ማጥፋት ዠመቻ መክፈት ሞክሯል ። የዚህ ፀሐፊ ማንነት ብናጠናው በኦሮሞ መጠሪያ ስም የተጠቀመ የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት ወገን የሆነ ወይም ህልናውን ለገንዘብ እና ለቁስ ነገሮች የሸጠ ከሐዲ አልያም የኦሮሞ ሕዝብ ታርክ ፣ቋንቋ ፣ ባህል የማያውቅ የኦሮሞ ሕዝብ ፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች አጥብቆ የሚቃወም ሰው ሊሆን ይችላል ።
ይህ ፀሐፊ ያለውን ቁንፅል ዕውቀት ተጠቅሞ በፃፈው ፁሑፍ ውስጥ "ጁሃር መሐመድ በአባቱ እስላም ኦሮሞ ስሆን በእናቱ ክርስቲያን አማራ ሆኖ እራሱን የኦሮሞ ሕዝብ ተቆርቋሪ ማድረግ የለበትም እንዲያውም ለጁሃር መፈጠር የእናቱ ድርሻ ከፍተኛ ስለሆነ መወገን የነበረበት ለእናቱ ነው "በማለት በግልፅ ማንነቱን እንድናውቀው ረድቶናል ።
ይህ ፀሐፊ በዚህ አላበቃም "ጁሃር መሐመድ ዓላማው የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ በሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ተጠቅሞ የእስልምና ሃይማኖት ማስፋፋት ድብቅ አጀንዳ እያራመደ ነው ።ለዚህ ማሳያ ደግሞ የአረቦች ጣቢያ በሆነው አልጀዚራ ቴሌቪዥን ላይ ቀርቦ "I am oromo First "ማለቱ ነው "ብሏል ። ቀጥሎም ጁሃር መሐመድ በእናቱ ክርስቲያን አማራ ሆኖ ሳለ እንዴት ሆኖ I am oromo First ልል ቻለ ብሎ ጠይቋል ።
ይህ ሰው ማለቴም ፀሐፊው የጁሃር ኦሮሞ መሆን አልተዋጠለትም ይህ ደግሞ ፀሐፊው እነ ጁሃር መሐመድ እያራመዱት ያለውን የኦሮሞ ነፃነት ትግል የማይፈልግ እና በነፃነት ትግሉን ለማደናቀፍ የቆሙ የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት ወገን መሆኑን በገሃድ አሳይቷል ።
ይህ ፀሐፊ ዋና እላማው ለኦሮሞ ውዱ እና ብርቅዬ የሆነ ጁሃር መሐመድ እና ጁሃር መሐመድ እየታገለለት ላለው ኦሮሞ ላይ ነው ። ጁሃር መሐመድ 45 ሚሊዮን የሆነው የኦሮሞ ልጆች የሚንወደው እና የሚናከብረው ውዱ እና ብርቅዬ ልጃችን ነው ። ጁሃር የሚታገለው ለኦሮሞ ብቻ አይደለም ጁሃር የሚታገለው ለአማራው ፣ ለጉራጌው ፣ ለአፋሩ ፣ ለሱማሌው ፣ ከጋምቤላው ፣ ለጉሙዙ ፣ ለወላይታው ፣ ለአደረው ፣ ለአድያው ለጌድኦው ...እና ለሌሎቹም በጭቆና እና በአንባገነናዊ ሥርዓት ሥር በመማቀቅ ላሉት ሕዝቦች ነው ። የጁሃር መሐመድ ዓላማ ግልጽ እና የጠራ ነው ።ጁሃር በነፃነት ትግል ውስጥ የመጀመሪያ አማራጭ ሰላማዊ ትግል ብቻ እንደሆነ ያምናል ።ጁሃር መሐመድ በነፃነት ትግል ውስጥ የትጥቅ ትግል የመጨረሻ አማራጭ ሊሆን ይችላል ብሎ የሚያምን በሳል ፖለቲከኛ ነው ። ይሁን እንጂ ይህ ፀሐፊ ጁሃር መሐመድ የእስልምና ሃይማኖት ለማስፋፋት በኦሮሞ ህዝብ ስም የሚጠቅም ሃይማኖተኛ አስመስሎ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍቶበታ ። ይህ ፀሐፊ አያቶቹ የዛሬ 100 ዓመት በፊት ስያራምዱት የነበረውን የኦሮሞ ሕዝብ ሃይማኖት ፣ ታርክ ፣ ቋንቋ ፣ ባህል የማጥፋት ሰፊ ዘመቻ እየደገመ ነው ።
ጁሃር መሐመድም ሆነ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የነፃነት ጥያቄ ነው ። የነፃነት ጥያቄ ደግሞ መልስ ማግኘት አለበት ። ጁሃርም ሆነ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ መልስ እስክያገኝ ድረስ የነፃነት ትግሉ በመጀመሪያ በሰላማዊ ትግል ይቀጥላል ። በሰላማዊ ትግል መልስ ካላገኘ ነፃነት የሕልውና ጉዳይ እና ጊዜ ሊሰጠው የማይችል ጉዳይ ስለሆነ ትግሉ በመጨረሻ አማራጭ በሆነው በትጥቅ ትግል ይቀጥላል ።
ጁሃር መሐመድ ኦሮሞ ነው ትግሉም የኦሮሞ ነፃነት ትግል ነው ። ውሻ በበላችበት ነው የሚትጮህ ።
Wellcome to the official blogger page of getachewbulti. This is getachewbulti official blogger page. Dedicated to posting my ideas,pictures, videos & vines of ethiopian's to show off our beauty and culture contributions are Wellcome.
Sunday, 15 February 2015
ውሻ በበላችበት ነው የሚትጮህ
Location:
Horn of Africa, null
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment