አገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት 20(ሃያ) ዓመታት ውስጥ ዘርፈ- ብዙ የልማት ዕድገት በማስመዝገብ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም አገር በአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ስነገረን ከርሟል ። ኢትዮጵያ ካስመዘገበችው ዕድገት ውስጥ ዋነኛው የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ዋነኛው ነው ።እነሱም የመንገድ ፣ የትምህርት ቤት ፣ የጤና ፣ የመጠጥ ውሃ ፣ የኃይል አቅርቦት ፣ የግብርና እና ሌሎችም የሚጠቀሱ መሰረተ ልማት ዕድገት በማስመዝገብ ረገድ የማይናቅ ሥራ ተሰርቷል ። በተለይ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የመንግሥትን ሥልጣነ በትሩን ከተቆናጠጠ ከ1983 ወዲህ አገርቷ የነበራትን 600 እስከ 800 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ሀብቷ በአሁኑ ጊዜ ታላቁን የሕዳሴ ግድብ ሳይጨምር ወደ 3500 ሜጋ ዋት አከባቢ አድርሳለች ።ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠቱን ስጀምር ይህ አገራችን ኢትዮጵያ አሁን ያላትን የኤሌክትሪክ ኃይሏን ወደ 10,000 ሜጋ ዋት ያድጋል ። በዚህ የኤሌክትሪክ ኃይል ሃብታችን በአፍሪካ ቀዳሚ ከማድረጉም በላይ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ከሃይሉ ሽያጭ ሊያስገኝልን እንደሚችል የብዙዎቻችን ግምት ነው ። በዚህ መጣጥፌ ስለአገራችን የኤሌክትሪክ ኃይል ሃብት ለመመስከር ፈልጌ ሳይሆን የዚህ ሃብት ባለቤት የማይቀረፍ ችግር የህዝቦቿ ብሶት እየሆነ መምጣቱን ለመግለጽ ፈልጌ ነው ። ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው በተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ምክንያቶ
No comments:
Post a Comment