የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲነት በምን ይገለፃል ?
ፕሎዎድን የተባለ አንድ የታርክ ፀሐፊ የገዳ ሥርዓት ማንነት ስገልፅ "Among the Republican system ,Gada is superior "ትርጉሙም "ከማንኛውም ሪፑብልካዊያን በበለጠ ገዳ የበላይ ነው ።"ማለቱ ነው ።ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሠም ይህንን ሃሣብ ስያጠናክሩ "Gada System is one of the most astonishing & instructive turns the evolution of human society has taken "ትርጉሙም "የገዳ ሥርዓት በሰው ልጅ ዕድገት (evolution )ውስጥ አስደናቂ የሆነ ብዙ ታላላቅ ለውጦች የታየበት ሥርዓት ነው "በማለት ይገልፃል ።
ባክስታር የተባለ ፀሐፊ "ኦሮሞ አስደናቂ የገዳ ሥርዓት ቢኖረውም ዕድሜያዊ መዋቅር (age sets) የሆነ አስተዳደራዊ ሥልጣን የሌለው ፣ በፖለቲካዊ ጉዳዮች በቀጥታ የማይገናኝ ፣ በአስተዳደራዊ ጉዳይ ውስጥ ምንም ዓይነት ድርሻ እንደሌለው እና ግጭትን መፍታት እንደማይችል ይናገራል ።ይሁን እንጂ ብዙ ፀሐፊዎች ከባክስታ ሃሳብ ጋር አይስማሙም ።ምክንያቱም በገዳ ሥርዓት ውስጥ የሚገኙ የዱባሌ ፣ ታናናሽ ጋሜ ፣ ታላላቅ ጋሜ ፣ ኩሳ እና ራባ ገዳ የተባሉ ደረጃዎች ሳያልፍ ወደ አባገዳ ሥልጣን የሚመጣ አንድም የኦሮሞ ልጅ አይኖርም ።እነዚህ የገዳ ሥርዓት እርከኖች ለሥልጣን የሚታጩ ሰዎች ልምድ እንድያገኙ እና የገዳ ሥርዓት ሃላፊነት መሸከም እንድችሉ እና ራሳቸውን የሚያዘጋጁበት አድካም (rite of passage )ያለው እና በዓለምአቀፍ የተደነቀ ሥርዓት ነው ።
Wellcome to the official blogger page of getachewbulti. This is getachewbulti official blogger page. Dedicated to posting my ideas,pictures, videos & vines of ethiopian's to show off our beauty and culture contributions are Wellcome.
Sunday, 1 February 2015
የገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲነት በምን ይገለፃል?
Labels:
History
Location:
Horn of Africa, null
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment