ሚካኤል ፋራዳይ ለማስታወስ ይሆን?
ውድ ወዳጆቼ እንደምን ውላችሁ ሰነበታችውልኝ? ዛሬም የጋራችን ጉዳይ እና የሁላችን ችግር የሆነውን የመብራት እና የኔትወርክ ጉዳይ አስመልክቶ አንድ መጣጣፍ ይዤላችሁ መጥቻለሁ ።
የዚህ ሁለቱ መሰረተልማት አገልግሎቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ መደበኛ እና የማይፈታ ችግር የዘንድሮው ከወትሮው በተለየ አኳኃን እየባሰበት መሄዱ ህብረተሰቡን ማማረር ሥራዬ ብሎ የተያያዘ ይመስላል ። ይህንን ችግር በቅርቡ እንደሚፈታ ጠቅላይ ሚንስትር እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት በተለያየ ጊዜ መግለጫ ቢሰጡም ችግሩ እየባሰበት ሄዶ ዘንድሮ የተለየ ሆኗል ። በተለየ መብራት ከዛሬ ሁለት እና ሦስት ዓመት በፊት የነበረው ችግር የሃይል እጥረት ስለሆነ የተጀመሩ እና በመጠናቀቅ ላይ ያሉት ግድቦች አገልግሎት መስጠት ስጀምሩ ችግሩ ይቀረፋል ተባለ ። እኛም አምነን መጠባበቅ ጀመርን ገልገል ጊቤ ቁጥር ሁለት ግድብ ተጠናቀቀ ችግሩ ግን አለ ፣ተከዜ ግድብ ተጠናቀቀ ችግሩ አልተቀረፈም ፣ ጣና በለስ ግድብ ተጠናቀቀ ችግሩ ግን አልተጠናቀቀም ። እንግዳው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እና የገልገል ጊቤ ቁጥር ሦስት ግድብ መጠናቀቅ ችግሩን ላይፈታው ይችላል ። አንድ ወዳጄ ይህንን የመብራት መቆራረጥ ችግር አስመልክቶ ስቀልድ "አሜርካኖች መብራትን የፈለሰፈውን ሚካኤል ፋራዳይ ለማስታወስ በዓመት ውስጥ ለሁለት ሰዓት መብራት ያጠፋሉ " ብሎ ሲጨርስ አንዱ ቀበል አድርጎ "ኢትዮጵያ ውስጥ በቀን ለ20 ሰዓታት የሚጠፋው ሚካኤል ፋራዳይ በእናቱ ኢትዮጵያዊ ይሆን ታዲያ "በማለት ይቀልዳሉ ።
ያም ሆነ ይህ የአገራችን የመብራት መቆራረጥ ችግር ምክንያቱ ባይታወቅም በቀን ለ20 ሰዓታት መጥፋቱ የተለመደ ጉዳይ ሆኖአል ።
ሌላው የኔትዎርክ ጉዳይ ሌላ እንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኗል ። ኔትወርክ ችግር ምን እንደሆነ ከመጀመሪያው ዓለም ከሰባ ዓመታት በፊት ሥራ ላይ አውለው ስጠቀሙበት የነበረውን ቴክኖሎጂ ቻይና ካገራ ነቅላ አምጥታ የተከለችው አሮጌ ቴክኖሎጂ በመሆኑ ከአገራችን ሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች ቁጥር ጋር ልመጣጠን አልቻለም ። የኔትዎርክ ችግራችን ከ2000 ሚሌኒየም በፍት ስልክ ለሰው ስትደውል "የደወሉለት ደንበኛ ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ ነው " የሚትለን ኮሚፒዩተር ተሻሽሎ ከ2000 ሚሌኒየም ወደዚህ ወደ"የደወሉለት ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም እባክዎ ትንሽ ቆይተው ይሞክሩ "ተቀይሮአል ። ስለ ኔትወርክ ችግር አንድ ወዳጄ ያጋጠመውን ስያስታውስ እንዲህ በማለት ይገልፃል "አንድ ጓደኛዬ ከዩኒቨርስቲ በድግሪ ስለተመረቀ በምርቃቱ ላይ መገኘት ስለአልቻልኩ ስልክ ደውዬ እንኳን ደስ አለክ ለማለት ስልክ ብቀጠቅጥ ኮሚፒዩተሯ የደወሉለት ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም እባክዎ ትንሽ ቆይተው ይሞክሩ ስትለኝ ከመበሳጨት የተነሳ ዓይነሽ ይጥፋ አንቺ ስትፈቅጂልኝ ብቻ ነው ከሚፈልገው ሰው ጋር የሚገናኘው አልኳት "በማለት ይቀልዳል ። አንዱ ጓደኛዬ ይህንን የኔትዎርክ ችግር ሲገለፅ እንዲህ አለኝ እኔም ለአንድ ጓደኛዬ ከዩኒቨርስቲ በድግሪ ስለተመረቀ በምርቃቱ ላይ መገኘት ስለአልቻልኩ ስልክ ደውዬ እንኳን ደስ አለክ ለማለት ስልክ ስደውል ማግኘት ስለአልቻልኩ መልህክት (SMS) አድርገለት መልህክቱ ሳይደርስ አየር ላይ ለሳምንት ቆይታ ከሳምንት ቦኋላ መልህክቱን የላኩለት ሰው እናቱ ሞተው ቀብር ላይ እያለ እንኳን ደስ አለክ ብዬ የላኩለት መልህክት ደረሰው መልህክቱ የተላከለት ሰው በጣም ገርሞት እናቴ መሞቷ ደስ ብሎኝ ነው ይህንን መልህክት የሚልክልኝ በማለት እንደተቀያየሙ አዉግቶልኛል ።
ስለዚህ የአገራችን ማህበራዊ አገልግሎቶች ችግር እየባሰበት መሄዱ አሳሳቢ እና ወቅታዊ የሆነ እልባት የሚሹ ሆኗልና በአፋጣኝ ይታሰብበት ።
Wellcome to the official blogger page of getachewbulti. This is getachewbulti official blogger page. Dedicated to posting my ideas,pictures, videos & vines of ethiopian's to show off our beauty and culture contributions are Wellcome.
Wednesday, 11 February 2015
ሚካኤል ፋራዳይ ለማስታወስ ይሆን?
Labels:
social problem
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment