ውድድሩ ሳይጀመር ተጠናቀቀ
አገራችን ኢትዮጵያ በ1983 የመንግሥት ለውጥ ካደረገች ቦኋላ በኢህአዴግ ዋና ተዋይነት እነሆ ድፍን 24 ዓመት ሞልቷታል።የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ቀድሞ የነበረውን ሥርዓት በጠመንጃ አፈሙዝ ከሥልጣን ካባረረው ቦኋላ የመንግሥትን ሥልጣነ ተቆጣጥሯል ።
ኢህአዴግ ከቀድሞ ሥርዓት የተለየ ርዮተዓለም በመያዝ የመጣ በመሆኑ ቀድሞ በነበረው የደርግ ሥርዓት አረመኔያዊ አገዛዝ አንፃር ኢህአዴግ ይዞ ብቅ ያለው ርዮተዓለም የተሻለ በመሆኑ በሥልጣን ላይ እንዲቆይ ምክንያት ሆኖለታል።
ኢትዮጵያ አገራችን ከ983 ዓመተምህረት ጀምሮ በኢህአዴግ መራሹ መንግሥት መተዳደር ከጀመረች ወዲህ ባለፉት 24 ዓመት ውስጥ አራት ጊዜ አገርአቀፍ ምርጫ አድርጋ አምስተኛ ዙር ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ትገኛለች ።
ያለፉትን አራቱን ዙር ምርጫ ኢህአዴግ በአሸናፊነት ስያጠናቅቅ አምስተኛውን ዙር ምርጫ ከወዲሁ ሻምፕዎንነቱን አረጋግጧል ። ኢህአዴግ ይህንን አምስተኛ ዙር ምርጫ በበላይነት ካጠናቀቀ የብራዚል ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በዓለም ዋንጫ የያዘውን ሪከርድ ይጋራል ።
እንዲያውም ብራዚል የዓለም ዋንጫን በተከታታይ ስላላነሳች የሪከሪዱ ብቸኛው ባለቤት ኢህአዴግ ብቻ ይሆናል ።
ኢህአዴግ ለ5ኛ ጊዜ መመረጥ የለበትም የሚል አቋም የለኝም ።የእኔ ጥያቄ ከኢህአዴግ ጋር ወደ ውድድር የገቡት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ውድድሩን ሳይጀምሩ ለምን አጠናቀቁ? የሚል ጥያቄ ነው ።
እነዚህ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጠንካራ ተወዳዳሪ መሆን አለመቻላቸው ምክንያት ብዙ ቢሆንም አንዱን ምክንያት ከአንድ የእግር ኳስ ቡድን ጋር አመሳስለን እንየው ።
በየትኛውም አህጉር ውስጥ ያለውን የአገሩን ፕርይሜሪ ሊግ ውድድር ውስጥ የሚካፈል አንድ ቡድን ውድድሩን በበላይነት ለማጠናቀቅ የሚችለው ክለቡ ጠንካራ የፋይናንስ አቅም ፣ የተደራጀ የሥራ አመራር ኮሚቴ ፣ ምርጥ አሰልጣኝ ፣ ሙሉ ተጫዋቾች ደጋፊዎች እና ሌላም ነገሮች ስኖሩት ነው ።
የአገራችን ተቃዋሚዎች በምንም መልኩ ጠንካራ ተወዳዳሪ መሆን አለመቻላቸው ምክንያት ከዚህ የእግር ኳስ ቡድን ጋር ይመሳሰላል ።
ስለዚህ እነዚህ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ውድድሩን ለማሸነፍ የሚችሉት
1ኛ, የሠለጠኑ አገራት የሚከተሉትን ርዮተዓለም መያዝ ይኖርባቸዋል
2ኛ,ተግባራዊ መሆን የሚችል ፓሊሲ መንደፍ
3ኛ,የብሔር ብሔረሰብ እና ህዝቦች እኩልነት መቀበል
4ኛ,የዓላማ ጽናት ያለው አባልና ደጋፊ በመመልመል ተከታታይ ሥልጠና በመስጠት አቅም መገንባት
5ኛ,የድርጅቱን አቋም በየጊዜው መፈተሽ እና ማስተካከያ እርምጃዎች መውሰድ እና ሌሎችም ስራ በመስራት መጠናከር አለባቸው ።
Wellcome to the official blogger page of getachewbulti. This is getachewbulti official blogger page. Dedicated to posting my ideas,pictures, videos & vines of ethiopian's to show off our beauty and culture contributions are Wellcome.
Monday, 2 February 2015
ውድድሩ ሳይጀመር ተጠናቀቀ!
Labels:
politics
Location:
Horn of Africa, null
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment