7ቱ የንስር ሕጎች
ንስሮች እጅግ ከፍ ያለ እና በየትኛውም የወፍ ዝርያ ሊደርስበት የማይችልበት ከፍታ ላይ ብቻቸውን ይበራሉ ።ንስር ከንስር ጋር በከፍታ ቦታ ላይ እንደሚበር ሁሉ አንተም ከብጤዎችህ ጋር መገኘት የሚገባህ ሥፍራ እና ከፍታ ላይ ብቻ ተገኝ ።የማይመጥንህ ሥፍራ አትገኝ ስፍራህ ከፍታ ነው።ንስር የሚበረው በከፍታ ከንስር ጋር ብቻ ነው አንተም ከማይመጥንህ ሰዎች እና ሥፍራ ተጠበቅ ።
2 ንስሮች እጅግ የጠንካራ እና የአስደናቂ እይታ ባለቤቶች ናቸው ።እስከ 5ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ አጣርቶ የማየት አቅም አላቸው ።አንድ ነገር ለመንጠቅ እያዩ መብረር ከጀመሩ የትኛውም ዓይነት ችግር እና እንቅፋት ብገጥማቸውም ታዳኙን እስክይዙ ድረስ እይታቸውን ከታዳኙ ላይ አይነቅሉም ።አንተም እይታ/ራህይ ይኑሪህ ምንም ዓይነት ችግር ቢፈጠር ከራህይ ወደ ኋላ አትበል ።
3 ንስር የሞተ ነገር አይመገቡም ልጆቹንም የሞተ ነገር አይመግበውም ጥንብ አንሳ እንጂ ንስር በፍጹም የሞተን ነገር አይወድም ።አንተም እንዲሁ ራስህን ምን እንደምትመግብ ተጠንቀቅ ። በተለይም ለጆሮ እና ዓይንህ ምን እንደምትመግብ ተጠንቀቅ ። በእጅህ ያሉት የሚትመግባቸው ነገሮች ሁልጊዜ አድስ እና የወቅቱን ሁኔታ የጠበቀ ይሁን ።የዱሮ ዕውቀትህ ለዛሬው ተመጋቢ ላይጠቅም ስለሚችል ሁልጊዜ ዕውቀትህን አድስ ።
4 ንስሮች ማዕበልን እጅግ ይወዳሉ ።ደማናዎች ስከማቹ ንስሮች ይደሰታሉ ማህበል የሚያስነሳውን ብርቱ ነፋስ ራሳቸውን ከደመናት በላይ ወደ ከፍታ በማውጣት ይጠቁሙበታል ይህ ደግሞ ክንፋቸውን እንዲያሳርፉ ይረዳቸዋል ። በዚህ ጊዜ ሌሎች የወፍ ዝርያ ሁሉ ግን ከዛፎች በታች ይጠለላሉ ።ማዕበሎቻችን ወደ ከፍታችን የመውጫ መስላሎቻችን ናቸው ። ተግዳሮቶችህን ወደ ከፍታው በማውጣት ተጠቀምበት ።
5 ንስር አንድን ነገር ከማመኑ በፍት ማረጋገጥን ይፈልጋል ።ሴቷ ወንዱን ከመገናኘቷ በፊት በእውነት እንደሚወዳት ለማረጋገጥ ትፈትነዋለች ።ራሷን ወደ ትልቅ ከፍታ ላይ ካወጣች ቦኋላ ክንፎቿን ሰብስባ ወደ መሬት ትወድቃለች ። በዚህ ጊዜ ወንዱ በፍጥነት ወደ ታች ተወርውሮ ካልያዛት መሬት ለመድረስ ጥቂት እስክቀራት ድረስ ትወረወራለች ።ያን ጊዜ ወንዱ ካልያዛት እና ካላነሳት መሬት ሳትደርስ አፋፉ ላይ ራሷ ትነሳለች ።በቃ ወንዱ ባል ልሆንላት አይችልም ማለት ነው ።አንተም በግል ፣ በአገልግሎት ፣ በማህበራዊ እንዲሁም በመንፈሳዊ ሕይወትህ የመሰጠትህን መጠን ሌሎች ቼክ ከማድረጋቸው በፊት ብቁ መሆንህን አረጋግጥ ።
6 ሴቷ ንስር እንቁላል የመጣያዋ ጊዜ ስደርስ ከወንዱ ጋር በጋራ በመሆን የተለየ እና የትኛውም የወፍ ዝርያ ሊደርስበት በማይችል ከፍተኛ ስፍራ ላይ ቦታ በማዘጋጀት ወንዱ ወደ ምድር በመውረድ መጀመሪያ እንጨት በማምጣት ይነጥፋል በመቀጠል እሾክ አምጥቶ ካነጠፈ ከዚያም ሣር ይጎዘጉዛል ።በዚህ መሰረት ሴቷ ንስር እንቁላል ጥላ ትታቀፋለች ጫጩቶች ከፈለፈለች ቦኋላ ጫጩቶቿን በረራ ታለማምደዋለች ።ጫጩቶቿን በረራ የምታለማምደው ጫጩቶቿን ከጎጆው ውስጥ ወደ ውጭ ገፍታ ካስወጣቻቸው ቦኋላ ጫጩቶቹ ተመልሶ ይመጣሉ ።በመቀጠልም ጫጩቶቿን ከጎጆው ውስጥ ገፍታ ካስወጣቻቸው ቦኋላ በጎጆው ውስጥ ያሉትን ሣሮች እና ሌሎች ለስላሳ ነገሮች ጉዝጋዞችን ታነሳዋለች ።ይህን ጊዜ ጫጩቶቹ ወደ ጎጆው ስመለሱ እሾክ ስለምወጋቸው ወደ ጎጆው መመለሱን ትተው ወደ ምድር ይወድቃሉ ።በሚወድቁበት ጊዜ ወንዱ/አባትዬው እየተከተለ እጠብቃቸዋል ።ለመውደቅ ጥቅት ስቀራቸው አንስቶ እንደገና ወደ ከፍታው በማውጣት ይለቃቸዋል ።መብረር መቻላቸውን ዕርግጠኛ እስከሚሆን ይህንን ተግባሩን ባለማቋረጥ ይፈፅማል ።የጎጆው ዝግጅት ለለውጥ መዘጋጀት እንዳለብን ያስተምረናል ።የወንዱ እና የሴቷ ንስሮች ትብብር እና የጋራ ሥራ ባለትዳሮች በቤታቸው እና በልጆቻቸው ጉዳይ የጋራ ሃላፊነት እንዳለባቸው ያሳየናል ።የጎጆው እሾክ እና የጫጩቶቹ እርምጃ መሄድ እና መንቀሳቀስ ስገባን አንድ ቦታ ለተወዘፍን የሚዋጋ እሾክ ከመምጣቱ በፊት ወደ ትክክለኛው ስፍራችን መገኘት እንዳለብን የሚያሳየን ክስተት ነው ።
7 ንስር ዕድሜው ስያረጅ የክንፉ ላባዎቹ እንደቀድሞው ብርቱ መሆኑ ይቀርና ደካማ እና ከፍ ብሎ መብረር የሚያቅተው ይሆናል ።ይህንን ስረዳው ወደ ሩቅ እና አለታማ ወደ ሆነው ስውር ቦታ በመሄድ ፍፁም እርቃኑን እስክቀረው ድረስ ላባውን ከላይ ላዩ እየነቀለ ያራግፋል ።ከዚህ ቦኋላ አድስ ላባ ተመልሶ እስክያበቅል ድረስ እዛው ስውር ቦታ ይቆያል ።አንተም ሁልጊዜ የአሮጌውን ሰው ባህሪ እና ልምምድህን ለአድሱ ማንነትህ እና ለእግዚአብሔር መንግሥት ስለማይሆን የምትከፍለውን ዋጋ በመክፈል አስወግደው ።
Wellcome to the official blogger page of getachewbulti. This is getachewbulti official blogger page. Dedicated to posting my ideas,pictures, videos & vines of ethiopian's to show off our beauty and culture contributions are Wellcome.
Monday, 9 February 2015
7ቱ የንስር ሕጎች!
Labels:
education
Location:
Horn of Africa, null
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment